መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 11፤2014-በኢትዮጵያ በእብድ ውሻ በሽታ በዓመት ከ2700 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን የሚያጡ ሲሆን ከአፍሪካ ከፍተኛ መሆኑ ተነገረ

በኢትዮጵያ የእብድ ዉሻ በሽታ ቀላል የማይባል ጉዳቶች እያስከተለ መሆኑን በህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የእንስሳት ነክ በሽታዎች ምርምር ቡድን መሪ ዶክተር ይመር ሙሉጌታ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡አሁን ላይ ባለው አሀዛዊ መረጃ መሰረት በኢትዮጲያ በዓመት 2700 ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ ህይወታቸዉን እንደሚያጡ ቢገለጽም ቁጥሩ ከዚህም ሊልቅ እንደምችል ባለሙያው ጠቁመዋል፡፡

የእብድ ውሻ በሽታ በበሽታው በተለከፉ እንስሳት ንክሻ ከውሻ፣ ድመት፣ ቀበሮ፣ ተኩላና ሌሎች ወደ ጤናማ ሰው ሊተላለፍ የሚችል አደገኛ በሽታ ሲሆን ከሰዉ ወደ ሰው ሊተላለፍ የሚችልበት መንገድ ሰፊ መሆኑን ዶክተር ይመር ለብስራት ተናግረዋል፡፡ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ምልክቶቹ መታየት የሚጀምሩት የአለም ጤና ድርጅት ባስቀመጠው ገደብ መሰረት ከአንድ እስከ ሶሥት ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ ቢሆንም አሁን በሚታዩ መረጃዎች ይህ የጊዜ ገደብ ከሳምንት ባነሰ እና ከአመት በበለጠ ጊዜ ሊለያይ ይችላል ፡፡

የጊዜ ገደቡ የሚወሰነው የበሽታ አምጭ ረቂቅ ህዋስ ወደ ማዕከላዊ የነርቭ ስርዓት ለመድረስ የሚፈጅበት ርቀት ሲሆን በአንገት፣ በጆሮ እና በትከሻ አካባቢ ከተነከሰ በአጭር ጊዜ ምልክቱ ሊጀምር ይችላል፡፡ ከተነከሰበት ቦታ በተጨማሪ የተነከሰበት መጠንም ለዚህ ምክንያት ይሆናል፡፡ ምልክቶቹ ሰዎችን እስከመናከስ ሊያደርስ ይችላል፡፡

በሽታው ላለባቸው ሰዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ሁለት ዓይነት መድኃኒት ይሰጣል፡፡ በኢትዮጲያ በዋጋ ዝቅ የሚለው እና ለ18 ቀናት በእንብርት የሚሰጠው ሲሆን ለ3 ቀናት በክንድ የሚሰጠው ክትባት ውድ በመሆኑ በኢትዮጲያ እየተሰጠ አይደለም፡፡

ትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *