መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 12፤2014-በአዲስ አበባ ከ560 ኪ.ሜ በላይ የመንገድና የድሬኔጅ መስመሮች ዝርጋታ ሊከናወን ነው ተባለ !

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በተያዘው በጀት ዓመት 568 ኪ.ሜ ልዩ ልዩ የመንገድና የድሬኔጅ መስመሮችን ለመጠገን እቅድ መያዙን በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ እያሱ ሰለሞን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ባለስልጣኑ የክረምቱን ከባድ ዝናብ እና ረጅም ጊዜ ከማገልገላቸው የተነሳ ለብልሽት የተዳረጉ የአስፓልት መንገዶችን የጥገና ስራ በማከናወን ለተሻለ የትራፊክ አገልግሎት እያዘጋጀ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡

በተለይም ከዚህ በፊት ለፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ለመዘርጋት ሲባል ተቆፋፍሮ ለትራፊክ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ ሆኖ የቆየውን ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ቤተ መንግስት በሚወስደው 450 ሜትር የሚሆን የአስፋልት መንገድ በተያዘው ሳምንት መጀመሪያ ላይ መደበኛ የጥገና ስራ አከናውኖ ለትራፊክ ክፍት አድርጓል፡፡

ባለስልጣኑ ከዚህ በተጨማሪም በአገልግሎት ብዛት ለብልሽት ተዳርገው የነበረቱን ከፍል ውሀ- ዘውዲቱ ሆስፒታል እና ከሜክሲኮ አደባባይ- አፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት ድረስ የቀኝ መስመር የአስፋልት መንገዶች ጥገና አከናውኗል፡፡

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *