መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 14፤2014-በማሊ በተካሄደ የተቃዉሞ ሰልፍ ከፈረንሳይ ጋር አጋርነት በመቀነስ ከሩሲያ ጋር ትብብር እንዲጠናከር ተጠየቀ

በማሊ ዋና ከተማ ባማኮ ከሩሲያ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዲኖር ለመጠየቅ በተደረገው ሰልፍ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ተገኝተዋል፡፡ሰልፉ የተካሄደዉ በፈረንሳይ እና ማሊ መካከል ለቀናት ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ መካሄዱን ተከትሎ የማሊ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሩሲያ ልዑክ ጋር እየተነጋገረ ይገኛል፡፡

አደባባይ የውጡት ሰልፈኞች የማሊን የሽግግር መንግስት እንደሚደግፉ አስታዉቀዋል፡፡ፈረንሣይ እና የቀጠናዉ ሀገራት በማሊ በየካቲት ወር ምርጫን እንዲከናዉን እና ከሩሲያ ጋር ሊኖር የሚችለው ትብብር እንዲቀር ግፊት እያደረጉ ይገኛል፡፡

ሰልፉ የተዘጋጀው የርወሎ በተሰኘ ንቅናቄ ሲሆን የፈረንሳይ ጦር በማሊ ዉስጥ መቆየቱን ይህዉ ንቅናቄ ይቃወማል፡፡እ.ኤ.አ ከ2013 አንስቶ በሰሜናዊ ማሊ የጂሃዲስቶችን ጥቃት ለመከላከል በሚል ፈረንሣይ እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ወታደራዊ ዘመቻ በማሊ ጀምሯል፡፡

ሆኖም ግን ይህ ዘመቻ ዘጠኝ አመታትን ቢያስቆጥርም ያለ ውጤት አንዳችም ደህንነት ሊያስገኝ አልቻለም በሚል ክፉኛ እየተተቸ ይገኛል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *