መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 18፤2014-ሰሜን ኮሪያ ሚሳኤል ማስወንጨፏን የደቡብ ኮርያ ጦር አስታወቀ

ሰሜን ኮሪያ በዛሬዉ እለት በምሥራቃዊ የባሕር ዳርቻ አጭር ርቀት የሚምዘገዘግ የሚሳኤል ሙከራ ስለማድረጓ የደቡብ ኮሪያ ጦር አስታዉቋል፡፡ሙከራው የተካሄደው የሰሜን ኮሪያ አምባሳደር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ ላይ ፒዮንግያንግ የመከላከያ እና የጦር መሣሪያ የመሞከር መብትን ማንም ሊከለክላት እንደማይችል እየተናገሩ ባሉበት ወቅት ነዉ፡፡

በተያዘዉ ወር መጀመሪያ ፒዮግያንግ ሁለቱንም የባልስቲክ እና የክሩዝ ሚሳኤል ሙከራ ማድረጓ ይታወሳል፡፡ሆኖም ከቀናት በፊት ሰሜን ኮሪያ ከደቡቧ ጋር ለመወያየት ፈቃደኛ መሆኗን ገልጻ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

የአሜሪካ ጦር በዛሬዉ እለት በሰጠው መግለጫ ሚሳኤል ስለመወንጨፉ መረጃዉን እንደሚያውቅ ቢገልጽም ለአሜሪካ አጋሮች ግን ምንም ዓይነት የስጋት ማስጠንቀቂያን አልሰጠም፡፡የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ሙን ጃኢን የፒዮንግያንግ የሚሳኤል ሙከራ በስተጀርባ ያለውን ማንኛውንም ዓላማ እንዲተነትኑ የሴዑል ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *