መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 18፤2014-ስልጣናቸውን ስለሚለቁት አንጌላ ሜርኬል አጫጭር መረጃዎች

~ በአዉሮጳ ህብረት ሀገራት ታሪክ ለ16 ዓመታት ጀርመንን በመምራት ለረጅም ዓመት በስልጣን ላይ የቆዩ መሪ ያደርጋቸዋል፡፡መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርኬል በጀርመን ህዝብ ዘንድ ሙቲ እናታችን ተብለዉ ይጠራሉ፡፡

~ እ.ኤ.አ በ1954 በምዕራባዊ ጀርመን ሀምቡርግ የተወለዱት ሜርኬል እጅግ ወግ አጥባቂ ከሚባል ቤተሰብ የተገኙ ሲሆን የአስተዳደጋቸዉ ተጽእኖ በሚመሩት ወግ አጥባቂዉ ፓርቲ ክርስቲያን ዲሞክራት ዩኒየን ዉስጥ ታይቷል፡፡

~ የፓለቲካዉን ዓለም በ35 ዓመታቸዉ የተቀላቀሉ ሲሆን ወቅቱ ደግሞ የጥል ግድግዳ የነበረዉ የበርሊን ግንብ የተደረመሰበት ነበር፡፡የበርሊን ግንብ የተደረመሰበት ቀን ለደስታ አንድ ቢራ መጎንጨታቸዉንና ሳዉና ዉስጥ ምሽቱን ማሳለፋቸዉን ተናግረዋል፡፡

~ ሜርኬል በፊዚክስ ዲግሪ እና በኳንተም ኬሚስትሪ የዶክትሬት የተቀበሉ ሲሆን በምሥራቅ ጀርመን የሳይንስ አካዳሚ በንድፈ ሃሳባዊ ኬሚስትሪ ክፍል ውስጥ ብቸኛዋ ሴት ነበሩ፡፡የልጅነት ህልማቸዉ የራሺያ ቋንቋ አስተማሪ የመሆን ነበር፡፡በመጨረሻም የፊዚክስ ሊቅ በመሆን ከሊፕዚግ ዩኒቨርሲቲ ፒኤችዲ አግኝተዋል፡፡

~ አንጌላ ሜርኬል በ1990ዎቹ በአንድ ውሻ ከተነከሱ በኃላ ጥልቅ የዉሻ ፍራቻ አድርሮባቸዋል፡፡ በ2007 በሩሲያ በነበራቸዉ ይፋዊ የስራ ጉብኝነት በቭላድሚር ፑቲን የግል ዉሻ ኮኒ እንዲደነግጡ መደረጋቸዉ በወቅቱ እንዳበሳጫቸዉ ተናግረዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *