መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 18፤2014-ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ በመሆን ተሹመዋል !

አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንግስት ምስረታ በዛሬው እለት የተከናወነ ሲሆን ፣ አዲስ ተመራጭ የምክር ቤቱ አባላት ስራቸውን ከመጀመራቸው አስቀድሞ ቃለ መሃላ በመግባት ጉባኤው ተጀምሯል፡፡

በዚህም መሰረት የብልፅግና ፓርቲ ለዋና አፈ ጉባኤነት ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር እጩ ሁኖ አቅርቧል፡፡

ምክር ቤቱም 138 በሆነ ድምፅ ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ በመሆን ሹሟል፡፡

ወ/ሮ ቡዜና 47 ዓመታቸው ሲሆን በቢዝነስ ማኔጅመንት የመጀመሪያ ድግሪያቸውን እንዲሁም በሊደርሺፕ ኤንድ ጉድ ገቨርነንስ ሁለተኛ ዲግሪ እንዳላቸው የትምህርት ዝግጅታቸው ያሳያል፡፡

በአሶሳ ከተማ የምክር ቤት አባል በመሆን አገልግለዋል እንዲሁም በህብረት ስራ ማህበራት ፣ ሴቶችና ህፃናት እንዲሁም በኢፌድሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዲኤታ በመሆን አገልግለዋል፡፡ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ፣ ሰራተኛውን አስተባብሮ በማሰራት በኩል አስቀድሞ በርካታ ስራዎች መስራት መቻላቸው በምክርቤቱ ተነግሯል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *