መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 18፤2014-የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ዊሃ 55ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን በማስመልከት በርካታ የማስታወቂያ ሰሌዳ በጎዳናዎች ላይ መሰቀሉ አነጋጋሪ ሆኗል

የላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ጆርጅ ዊህ ትላልቅ የቁም ፎቶ ያላቸው ቢልቦርዶች መስከረም 21 ቀን ከሚከበረዉ 55ኛው ዓመት የልደት ቀናቸው አስቀድሞ በዋና ከተማዋ ሞንሮቪያ ጎዳናዎች ላይ ተሰቅለዉ ይገኛሉ፡፡የልደት የማስታወቂያ ሰሌዳዎች በአሁኑ ጊዜ በመላው ሞንሮቪያ እና በሌሎች የከተማው ክፍሎች ላይ እየተሰቀሉ ይገኛል፡፡

በእያንዳንዱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ተመሳሳይ መልእክት ተጽፏል፡፡ “እርስዎ ፕሬዝዳንታችን የጥራት ተምሳሌት ስለሆኑ ሁሉም መሪዎች እንደ እርስዎ መሆን አለባቸው፤ መልካም ልደት በልብዎ ማዕዘን ውስጥ የተደበቁ ምኞቶች ሁሉ እንዲሟሉ እንመኛለን” የሚል መልዕክቱን ሰፍሮባቸዉ ተልጥፈዋል፡፡

የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ፕሬዚዳንቱ ይህ ይገባቸዋል በማለት የመሪያቸው ምስል በሁሉም ቦታ ተሰቅሎ በማየታቸው መደሰታቸዉን ተናግረዋል፡፡ነገር ግን ተቺዎች እንደሚሉት እንዲህ ዓይነቱ ወጪ የኢኮኖሚ ችግር ባለበት ወቅት እና አብዛኛው ህዝቧ ድሃ በሆነበት ሀገር ውስጥ ግዴለሽነትን ያሳያል ሲሉ ተቃዉመዉታል፡፡

ወጣቱ የሞንሮቪያ ከተማ ከንቲባ ጀፈርሰን ኮይጄ የልደቱን ቀን በደጋፊዎች በጎዳና ላይ ሰልፍ እና ምስሎቹን በማሰቀል በአስገራሚ ክስተቶች ካከበረ በኃላ በድጋሚ የጆርጅ ዊሃ ልደት በእንዲህ አይነት መልኩ መከበር መጀመሩ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *