መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 18፤2014-የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ባጋጠመው የድምጽ ስርዓት (sound system)ችግር ምክንያት የጥላሁን ገሰሰን የልደት በዓልን ጨምሮ በርካታ መርሃግብሮች ተሰርዘዋል

ቴአትር ቤቱ በየአመቱ የሚያከብረውን የዶክተር አርቲስት ጥላሁን ገሰሰን ልደትን እንዲሁም መስቀል በአልን ጨምሮ የመስከረም እሁዶች ላይ ይቀርብ የነበረው የሙዚቃ ዝግጅት በሳውንድ ሲስተም ችግር ምክንያት አለማቅረቡን የቴአትር ቤቱ የሙዚቃ ክፍል ሃላፊ አቶ ወሰንየለህ መብረቁ በተለይ ለብሰራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

የክቡር ዶክተር አርቲስት ጥላሁን ገሰሰ የልደት በዓል በየዓመቱ ይከበር የነበረ ቢሆንም ከ2011 ዓ.ም ወዲህ ላላፉት ሁለት አመታት እንዲሁም በዚህ አመት ጭምር የልደት በአሉ እንደቀደመው ጊዜ እየተከበረ አለመሆኑን አንስተዋል፡፡

የጥላሁን ገሰሰ ልደት እሰከ 2011 ድረስ ሲከበር ቢቆይም በ2012 ቤተሰቦቹ ባለመኖራቸው የብሄራዊ ቴአተር ሰራተኞች ለብቻቸው አስበውት ዉለዋል፡፡ ከዛ መልስ ታዲያ በ2013 የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ በነበረዉ አስገዳጅ መሰባሰብን በሚከለክለዉ መመሪያ ያለተከበረ ሲሆን በተያዘዉ 2014 አመት ደግሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ባጋጠመው የሳውንድ ሲስተም ችግር ምክንያት ሊከበር አልቻለም ብለዋል፡፡

የሳውንድ ሲስተም ችግሩ መኖሩ በየአመቱ ይካሄድ የነበረው ቴአትር ቤቱ ለአመታት ሲከውን የቆየውን የአዲስ አመት እሁዶች እና የመስቀል በአል የሙዚቃ ዝግጅትን እንዳይቀርብ እንቅፋት ሆኖበታል፡፡ይሄ ችግር ሊፈታ የሚችለው ሳውንድ ሲስተሙ እንዲሰራ በማድረግ ወይም በመጠገን ሳይሆን በአዲስ በመተካት ነዉ፡፡ ሆኖም ግን ግዢ ባለመፈጸሙ የሙዚቃ ከፍሉም ስራውን በአግባቡ ሊሰራ አለመቻሉን አቶ ወሰንየለህ ጨምረው ለብሰራት ሬዲዪ ተናግረዋል፡፡

ቤተልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *