መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 18፤2014-ግብፅ ዩቲዩበሮችን ግብር እንዲከፍሉ ለማድረግ ማቀዷ መነጋገሪያ ሆኗል

በግብፅ ዩቲዩበሮች ግብር እንዲከፍሉ የወጣዉ ዕቅድ የተለያዩ የድጋፍ እና የተቃዉሞ አስተያየቶች እንዲደመጡ አድርጓል፡፡የግብጽ የግብር ባለስልጣን ዩቲዩበሮች እና ጦማሪያን ዓመታዊ ገቢያቸውን እንዲያስመዘገቡ እና እንዲያሳውቁ ጠይቋል።

መንግስት በዋናነት ትኩረት ያደረገዉ በየዓመቱ ከ32,000 የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚያገኙትን እንደሆነም ተነግሯል፡፡በማህበራዊ ሚዲያ አንዳንድ ሰዎች አዲሱን የግብር መመሪያ ሲደግፉ ተስተዉለዋል፡፡

በማህበራዊ ገጽ ትስስር ላይ እየተንሸራሸሩ ካሉ ሀሳቦች መካከል አነስተኛ ገቢ ያላቸዉ የአትክልት ሻጮች ግብር ይከፍላሉ እኛ ሀብታሞቹ ዩቲበሮች ግብር ልንከፍል ይገባል ያሉም ተገኝተዋል፡፡የግብጽ የታክስ ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ሀላፊ መሐመድ አል ጌይርን በበኩላቸዉ በግብፅ ውስጥ ትርፍ የሚያገኝ ማንኛውም ሰው የሥራው መስክ ምንም ይሁን ምን በትክክል ግብር ይከፈልበታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሌሎች ደግሞ የበይነመረብ ወጪዎችን በመጥቀስ እርምጃውን ይቃወማሉ ፣መንግስት ዩቲዩቦችን ቀረጥ እንዲከፍሉ ከፈለገ ቢያንስ የተሻለ የበይነመረብ አገልግሎት ሊሰጠን ይገባል ሲሉ ተችተዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *