መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 20፤2014-አቶ ኡሞድ ኡጁሉ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተመረጡ

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አቶ ኡሞድ ኡጁሉን የክልሉ ርዕሠ-መስተዳድር አድርጎ መርጧል፡፡አቶ ኡሞድ ኡጁሉ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት፣ የክልሉ ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲሁም ከህዳር 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የክልሉ ርእሠ መስተዳድር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን ውጤታማ ሀላፊነትን የተወጡ አመራር መሆናቸው ተገልጿል።

በመሆኑም አሁንም ለቀጣይ አምስት አመታት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *