መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 25፤2014-ሱዳን በወደብ መዘጋት የተነሳ የመድሃኒት ፣ ነዳጅ እና ስንዴ ክምችቷ እያለቀ መሆኑን አስታወቀች❗️

በሀገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍል በቀጠለዉ ተቃዉሞ የተነሳ ዋንኛ የሀገሪቱ ወደብ በመዘጋቱ ምክንያት የሱዳን መንግሥት ለሕይወት አድን አስፈላጊ የሆኑ መድኃኒቶች ፣ ነዳጅ እና የስንዴ ክምችት እያለቀ መሆኑን አስጠንቅቋል።ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ከቤጃ ጎሳ የመጡ ተቃዋሚዎች በሱዳን ወደብ አቅራቢያ እና የቀይ ባህር ወደቦች እንዲዘጉ አስገድደዋል፡፡

ተቃዋሞዎቹ በዋናነት የሀገሪቱን ደካማ የኢኮኖሚ ሁኔታ ተችተዋል፡፡የመንግስት ካቢኔ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀዉ የምስራቃዊ ሱዳን ተቃዉሞ ትክክለኛነቱን በማመን የሰላማዊ ተቃውሞ መብትን አፅንዖት ሰጥቷል ፡፡ ነገር ግን የምስራቃዊ ሱዳን ክልል ከሌላው የሀገሪቱ ክፍል ጋር የሚያገናኙት ወደብ እና አውራ ጎዳናዎች መዘጋት የሁሉንም የሱዳን ግዛቶች ፍላጎት የሚጎዳ ነው ሲል አስጠንቅቋል።

ካቢኔው በምስራቅ ሱዳን ችግሮች ፖለቲካዊ መፍትሄ ላይ ለመስራት ቃል ገብቶ ሰልፈኞቹ ከመንግስት ጋር ውይይት እንዲጀምሩ ጥሪ አቅርቧል።ይሁን እንጂ የቤጃ ጎሳ አባላት በትላልቅ ድንጋዮች ወደ ወደብ የሚወስዱ መንገዶችን በመዝጋታቸው ከማዕከላዊው መንግስት ጥያቄ ጋር የሚስማሙ አይመስልም፡፡

ባለፈው ወር ተቃዋሚዎች ነዳጅን ወደ ዋና ከተማዋ ካርቱም የሚያጓጉዘውን ጨምሮ ሁለት ዋና ዋና የነዳጅ ቧንቧዎችን ዘግተዉ ነበር። መስከረም 26 ሰልፈኞቹ የወደብ አልባዋ ደቡብ ሱዳን ድፍድፍ ነዳጅ በቀይ ባህር በኩል ወደ ውጭ እንዲላክ ለመፍቀድ ተስማምተዉ ነበር፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *