መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 26፤2014-መንግስት በቦሌ እና ላፍቶ ክ/ከተሞች አጥሮ የያዛቸው ቦታዎች 6 መቶ ቢሊዮን ብር የሚገመቱ ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተናገሩ❗️

በአዲስ አበባ ሆነ በሌሎችም የሀገሪቱ ክፍሎች መንግስት በቴሌኮሚዩንኬሽን ፤ በመብራት እና በሌሎችም ምክንያቶች እያጠረ ያስቀመጣቸው መሬቶች ከፍተኛ የሆነ ክስተረትን እንደሀገር እያስከተለ ይገኛል ተብሏል ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በዛሬው እለት 6ኛ ዙር አንደኛ ዓመት አንደኛ ልዩ ስብሰባውን እያከናወነ ባለበት ወቅት ላይ የምክር ቤቱ አባላት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄዎችን አቅርበው ምላሽ እየተሰጠ ይገኛል ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ መሰረት በተለየ መልኩ በመንግስት ታጥረው እየባከኑ የሚገኙ የመሬት ሃብቶች መኖራቸውን አንስተዋል።

በቦሌ እና ላፍቶ ክ/ከተሞች በመንግስት ብቻ ታጥረው የሚገኙ መሬቶች ስድስት መቶ ቢሊዮን ብር የሚገመት ሃብት የያዙ ሲሆን ይህም እንዲባክን ሆኗል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የመኖሪያ ቤት እጥረት ባለበት ከተማ ውስጥ ይህ ችግር መታየቱ ተገቢ አይደለም ሲሉ አክለው ማንሳታቸውን ብስራት ከምክር ቤቱ የፓርላማ ውሎ ለመከታተል ተችሏል ፡፡

ናትናኤል ሀብታሙ !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *