መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 26፤2014-“የገጠሩ ማህበረሰብ ሲስቅ ነው ኢትዮጵያ መሳቅ የምትችለው” ሲሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ ተናገሩ

በዛሬዉ እለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ አመት 1ኛ ልዩ ስብሰባ እየተካሄደ ነው።

በስብሰባዉ ላይ አዲሱ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ ለገጠሩ የማህበረሰብ ክፍል ሁለንተናዊ ሽግግር ሊያሳካ የሚችል ተቋም አለመኖሩን ተናግረዋል።

የገጠር መኖሪያ ቤቶች ማሻሻያ መርሀግብር በመዘርጋት የገጠሩን ማህበረሰብ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባም ገልጸዋል ። አያይዘውም የገጠሩ ማህበረሰብ ሁለንተናዊ ሁኔታ መሻሻል ሲችል ነዉ እንደሀገር መሻሻል የምንችለው ሲሉ ተናግረው የገጠሩ ማህበረሰብ ሲስቅ ነዉ ኢትዮጵያ መሳቅ የምትችለው ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *