መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 28፤2014-ኬንያ ከሶማሊያ ጋር ያላት ክርክር ተከትሎ የፍርድ ቤት ውሳኔን ለመቀበል ፈቃደኛ እንዳልሆነች ተሰማ

ኬንያ ከሶማሊያ ጋር ያላት ክርክር ተከትሎ የፍርድ ቤት ውሳኔን ለመቀበል ፈቃደኛ እንዳልሆነች ተሰማ

ኬንያ ከሶማሊያ ጋር በባህር ጠረፍ የይገባኛል ውዝግብን በተመለከተ በሚቀጥለው ሳምንት የሚጠበቀውን የዓለም አቀፍ ገላጋይ ፍርድ ቤት እውቅና አልሰጥም ስትል አስታዉቃለች፡፡ በዚሁ ዙሪያ ጠንካራ መግለጫ ያወጣዉ የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተዛባ የፍርድ ሂደት ፍፃሜዉ ይሆናል ሲል አስታዉቋል፡፡

ኬንያ በሕንድ ውቅያኖስ 160,000 ስኩዌር የሚመለከተውን የህግ ሂደት ትክክለኛነት በመጠራጠር በዚሁ ዓመት መጀመሪያ ችሎቱን አቋርጣለች፡፡ አካባቢው በነዳጅ እና በተፈጥሮ ጋዝ የበለፀገ ነው መባሉ ሀገራቱን በይገባኛል እንዲወዛገቡ ምክንያት ሆኗል፡፡

የባህር ዳርቻው ልክ እንደ መሬት ድንበር በተመሳሳይ አቅጣጫ መከተል አለበት ስትል ሶማሊያ ጉዳዩን በ2014 ወደ ዓለም አቀፉ ገላጋይ ፍርድ ቤት እንዳመጣችዉ ይታወሳል፡፡ፍርድ ቤቱ በቀጣዩ ሳምንት ማክሰኞ ዉሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *