መደበኛ ያልሆነ

መስከረም 28፤2014-ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዐቢይ አሕመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሰየማቸውን ተከትሎ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።ፕሬዝዳንት ፑቲን በመልዕክታቸው የሩሲያ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት በመልካም የወዳጅነት እና እርስ በርስ መከባበር ላይ የተመሠረተ ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ በቀጣይም ለኢትዮጵያ የሚያደርጉት አስተዋጽኦ የበለጠ እንደሚጨምር አምናለሁ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ አክለውም የሩሲያ እና ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ትብብርን በተለያዩ ዘርፎች በማዳበር ለህዝቦቻችን ጥቅም እንሰራለን ብለዋል።ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባስተላለፉት መልዕክት ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ መልካም እና ስኬታማ የስራ ዘመን ተመኝተዋል።

መረጃው በኢትዮጵያ የሩሲያ ኤምባሲ ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *