መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 2፤2014-በ2014 በጀት ዓመት 88 የሞት አደጋ ያደረሱ አሽከርካሪዎች ታገዱ

በ2014 በጀት ዓመት 88 የሞት አደጋ ያደረሱ አሽከርካሪዎች ታገዱ

በ2014 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት በደንብ ቁጥር 395/2009 መሰረት የሞት አደጋ ያደረሱ 88 እንዲሁም ከባድ የአካል ጉዳት ያደረሱ 282 በድምሩ 370 አሽከርካሪዎች እንዲታገዱ ለፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣንና እና ለአዲስ አበባ ከተማ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዝርዝር መረጃ ተልኳል።በሌላ በኩል 512 አሽከርካሪዎች የተሃድሶ ስልጠና እንዲወስዱ ዝርዝራቸው መላኩን በትራንስፖርት ቢሮ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አረጋዊ ማሩ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል

ከባድ የአካል ጉዳትና የሞት አደጋ አድርሰው የተሀድሶ ስልጠናቸውን ካጠናቀቁ 438 አሽከርካሪዎች መካከል 347 አሽከርካሪዎች እግድና የተሃድሶ ስልጠና አጠናቀው መንጃ ፈቃዳቸው ተመላሽ ተደርጓል፡፡

የደህንነት ቀብቶን እና የህጻናት የደህንነት መደገፊያ በአሸከርካሪዎች መተግበሩን ቁጥጥር በማድረግ ህጉን ተላልፈው በተገኙ 924 አሽከርሪዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡

ከፍጥነት በላይ ባሽከረከሩ 23 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ሲወሰድ የኮቪድ 19 ለመከላከል ከመጫን አቅም ጋር ተያይዞ ለመቆጣጠር የወጣውን መመሪያ በማስተግበር ሂደት መመሪያውን የተላለፉ 32 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደተወሰደባቸው አቶ አረጋዊ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ቤተልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *