መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 4፤2014-ህብረተሰቡ ሴሬስ የአፕል ጭማቂ በውስጡ ጎጂ የሆነ ከሻጋታ የመነጨ መርዛማ ኬሚካል ስለተገኘበት ምርቱን እንዳይጠቀም ማሳሰቢያ ተሰጠ

ህብረተሰቡ ሴሬስ የአፕል ጭማቂ በውስጡ ጎጂ የሆነ ከሻጋታ የመነጨ መርዛማ ኬሚካል ስለተገኘበት ምርቱን እንዳይጠቀም ማሳሰቢያ ተሰጠ

በፍራፍሬዎች ላይ የሚከሰት ማይኮቶክሲን የተሰኘው ከሻጋታ የሚመነጭ መርዛማ ኬሚካል ሴሬስ የአፕል ጭማቂ 100 በመቶ(Ceres apple juice 100 % ) በተሰኘ ምርት ዉስጥ ስለተገኘ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ይሄ ምርት የዓለም አቀፍ የምግብ ደህንነት ማስጠንቀቂያ በአለም አቀፍ ደረጃ ምርቱ ጥቅም ላይ እንዳይውል ያስጠነቀቀ መሆኑን የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር አቶ አበራ ደነቀ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡በተመሳሳይ የዚሁ ምርት አምራች የሆነው የደቡብ አፍሪካ የምግብና የመጠጥ ኩባንያ ፓየኒር ምግቦች ማይኮቶክሲን የተሰኘው ከሻጋታ የሚመነጭ መርዛማ ኬሚካል በውስጡ በእንዳለ በመግለጽ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀመው ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፡፡

በኢትዮጲያ ገበያ ውስጥም ይህዉ ምርት እንዳለ በመገንዘብ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም እና በማንኛዉም አጋጣሚ ገበያ ላይ ሲገኝ በፌዴራል ደረጃ በነጻ ስልክ መስመር በ8482 እንዲሁም በአቅራቢያ ለሚገኙ የክልል ተቆጣጣሪ አካላት ጥቆማ ሊሰጥ ይገባል ሲሉ አቶ አበራ ደነቀ ጨምረዉ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

በትግስት ላቀዉ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *