መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 4፤2014-‹‹ህጋዊ ነን ቆጣሪ እናስገባላችኋላን›› በማለት ሲያስጭበረብሩ የነበሩ 3 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደንበኞቹን ድካምና እንግልት ለማስቀረት የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንድ የቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች በተለያዩ ምክንያቶች ቆጣሪያቸው ዘግቶ በአስቸኳይ ለማስነሳት ሲፈልጉ ፣ ህገ-ወጥ በሆኑ ግለሰቦች የማታለል ድርጊት ሲፈፀምባቸው ይስተዋላል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማም ሶስት ግለሰቦች በገርጂ እና በካሳንቺስ በተለያዩ አካባቢዎች ፣ መሰል ህገ-ወጥ ተግባራቸውን ሲያከናውኑ በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የህዝብ ግንኙነት ስራ አስኪያጅ አቶ በቀለ ክፍሌ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በመሆኑም ደንበኞች የቅድመ ክፍያ ቆጣሪ በሚዘጋበት ጊዜ ቆጣሪውን ባወጡበት የአገልግሎት መስጫ ማዕከል በአካል በመሄድና የኤሌክትሪክ ሃይል በማስሞላት ፣ ሌላ የቴክኒክ ባለሙያ ሳያስፈልጋቸው በራሳችሁ ካርድ ቆጣሪውን የምታስነሱበት ፍቃድ ማግኘት እንደሚችሉ አገልግሎቱ አስታውቋል፡፡

ህብረተሰቡ መሰል ህገ-ወጥ ድርጊት ፈፃሚዎች በሚያጋጥሙበት ወቅት ለሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት አልያም ለአገልግሎቱ ጥቆማ እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *