መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 4፤2014-የቦብ ማርሌይ ልጅ ጁሊያን ማርሌይ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ለማድረግ አዲስ አበባ ገባ

የቦብ ማርሌይ ልጅ ጁሊያን ማርሌይ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ለማድረግ አዲስ አበባ ገባ

የታዋቂዉ ሬጌ አቀንቃኝ ቦብ ማርሌይ ልጅ ጁሊያን ማርሌይ እና የሙዚቃ ጓደኞቹ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ለማድረግ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

የሁለት ጊዜ የግራሚ አዋርድ እጩ እና የሬጌ ንጉሱ ቦብ ማርሌይ ልጅ ጁሊያን ማርሌይ እና ጓደኞቹ በሳምንቱ መጨረሻ በጊዮን ሆቴል የሬጌ ኮንሰርት እንደሚያዘጋጁ አስታዉቀዋል። ከኮንሰርቱ ከሚገኘዉ ገቢም በኢትዮጵያ ላለዉ ሰብዓዊ ችግር ድጋፍ እንደሚያድርጉም ተገልጿል፡፡

ዝነኞቹን አቀንቃኞች ቱሪዝም ኢትዮጵያ ከአይዞን ፋዉንዴሽን ጋር በመተባበር ባደረገላቸዉ ግብዣ ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸዉን ከቱሪዝም ኢትዮጵያ የፌስቡክ ገጽ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *