መደበኛ ያልሆነ

ጥቅምት 4፤2014-የ15 ቀን ህፃን መፀዳጃ ቤት ውስጥ የከተተች ግለሰብ በቁጥጥር ዋለች።

የ15 ቀን ህፃን መፀዳጃ ቤት ውስጥ የከተተች ግለሰብ በቁጥጥር ዋለች።

ይህው ድርጊቱ በደጀን ከተማ 01 ቀበሌ ልዩ ቦታዉ ቀጠና 5 እየተባለ ከሚጠራዉ ቦታ ላይ ተፈፅሟል።

ተጠርጣሪ ግለሰብ ለምለም ዋለ የተባለችዉና የወረጃርሶ ወረዳ ፍልቅልቅ 01 ቀበሌ ነዋሪ የሆነችዉ ከተወለደ 15 ቀን የሆነዉን ህጻን ጥቅምት 3 ቀን 2014 ዓ/ም ከንጋቱ በግምት 12 ሰዓት ሲሆን መፀዳጃ ቤት ዉስጥ ከታዉ ትሰወራለች።

የቤቱ ባለቤት ከመኝታ ተነስታ ሽንት ቤት ስትጠቀም ከሽንት ቤቱ ዉስጥ ህጻኑ ሲያለቅስ ስትሰማ የድረሱልኝ ጩኸት በማሰማቷ የአካባቢዉ ማህበረሰብ ህጻኑን ከሽንት ቤት አዉጥቶ ለፖሊስ ሪፖርት አድርጓል።

የደጀን ከተማ ፖሊስ ወደ ቦታዉ ሄዶ ህጻኑን ደጀን ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ እንዲደረግለታ ያደረገ ሲሆን ፖሊስ አጥፊዋን ተከታትሎ በመያዝ ምርመራዉ በመጣራት ላይ እንደሚገኝ ብስራት ከደጀን ወረዳ ኮሚኒኬሽን ያገኘው መረጃ ያሳያል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *