መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 6፤2014-ለ26 ዓመታት በስህተት በግፍ እስር ላይ የነበረው ጥቁር አሜሪካዊ ይቅርታ ተደረገለት

ለ26 ዓመታት በስህተት በግፍ እስር ላይ የነበረው ጥቁር አሜሪካዊ ይቅርታ ተደረገለት

በሰሜን ካሮላይና ነዋሪ የሆነው አፍሪካ አሜሪካዊ የሆነው ዶንታ ሻርፕ አንድ ነጭ ገድሏል በሚል በስህተት ተከሶ ለ26 ዓመታት በእስር አሳልፏል።ዶንያ ሻርፕ ግን ከታሰረበት ጊዜ አንስቶ ንፁህ ሰው መሆኑን ለማረጋገጥ ታግሏል።

ጆርጅ ራድክሊፍ የተባለውን ግለሰብ እ.ኤ.አ በ1994 በመግደል የተከሰሰ ሲሆን የጥፈተኝነት ውሳኔ ላይ የ15 ዓመቷ ሻርሊን ጆንሰን በሰጠችው ምስክትነት ላይ የተመሰረት ነበር።ሻርሊን የሰጠችውን ምስክርነት ከሁለት ሳምንት በኃላ በመቀየር በመርማሪዎች መሳሳቷን ብትናገርም ውሳኔው ይፀናል።

ለ26 ዓመታት ይህ የተሳሳት ውሳኔ እንዲሻር ሻርፕ ባደረገው ትግል ጉዳዩ በ2019 በአንድ የከፍተኛው ፍርድ ዳኛ የጥፋተኝነት ውሳኔው እንዲነሳ ሆኗል።የሰሜን ካሮላይና ገዢ ሮይ ኩፐር ሙሉ ይቅርታ እንደተሰጠው በመግለፅ እንደ ሻርፕ ያለ በደላቸው የተቀጡ ሰዎች በይፋ እውቅና ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል።

ሻርፕ ከሰሜን ካሮላይና ግዛት ካሳ የመጠየቅ መብት እንዳለው ተነግሯል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *