መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 6፤2014-በሶማሊያ ሁለት የዩጋንዳ ወታደሮች የሞት ፍርድ ተበየነባቸው❗️

በሶማሊያ ከሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ወታደሮች ጋር በማገልገል ላይ ያሉ አምስት የዩጋንዳ ወታደሮች በነሀሴ ወር ሰባት ሰላማዊ ሰዎችን በመግደል ጥፋተኛ ተብለዋልከወታደሮቹ መካከል ሁለቱ የሞት ቅጣት የተፈረደባቸው ሲሆን ሶስቱ ወታደሮች ደግሞ በ39 ዓመታት እስር እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል።

ሶስቱ ግለሰቦች የእስር ጊዜያችወን እንዳጠናቀቁ ወደ ዩጋንዳ ይመለሳሉ ተብሏል።በሶማሊያ ጎልዌይን በወታደሮቹና በአልሻባብ ታጣቂዎች መካከል በነበረ የተኩስ ልውውጥ ንፁሃን በህገወጥ መንገድ መገደላቸውን የአፍሪካ ህብረት መግለፁ ይታወሳል።

የአፍሪካ ህብረት የአሚሶም ጦር በሶማሊያ ያለፉትን 14 ዓመታት ቆይቷ አድርጓል።ከአሚሶም 20ሺ ወታደሮች ውስጥ አንድ ሶስተኛው የዩጋንዳ ወታደሮች ናቸው።በወታደራዊው ፍርድ ቤት ውሳኔ መደሰታቸውን የተጎጂዎቹ ቤተሰቦች ተናግረዋል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *