መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 6፤2014-በአዲስ አበባ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት ከኅዳር 6 እስከ ኅዳር 15 ይሰጣል

በአዲስ አበባ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት ከኅዳር 6 እስከ ኅዳር 15 ይሰጣል

በአዲስ አበባ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት እድሜያቸው ከ12 ዓመት በላይ ለሆኑ ለሁሉም የከተማዋ ነዋሪዎች ከኅዳር 6 እስከ ኅዳር 15 መሰጠት መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ዮሃንስ ጫላ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ክትባቱ ለ10 ተከታታይ ቀናት በሚቆይ ሲሆን፤ ከ1 ሚሊየን በላይ ዜጎች በነጻ ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱን አስታውቀዋል።

ክትባቱ በመንግስት የጤና ተቋማት እና በጊዜያዊ የክትባት መስጫ ተቋማት ውስጥ እንደሚሰጥ የገለፁት ኃላፊው፤ ከጤና ጣቢያዎች በተጨማሪም በትላልቅ የገበያ ቦታዎች ፣ ሞሎች ፣ በባንኮች ፤ በትራንሰፖርት መናህሪያዎች ፤ በኢንዱስትሪ ፓርክ እና በሌሎች የተመረጡ ቦታዎች ም እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡

እስካሁን በከተማው በተደረገው ክትባት ከግማሽ ሚሊየን በላይ ዜጎች ክትባት መውሰዳቸውንና፤ በታቀደው መሰረትም በክትባት ዘመቻው 1 ሚሊየን የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ 777 የሚሆኑ የክትባት ቡድኖች አገልግሎት ለመስጠት መሰማራታቸውም አስታውቀዋል።

ስለሆነም የቫይረሱን ሥርጭት ለመቆጣጠርና ለመግታት ህብረተሱቡ ግንዛቤው ኖሮት እንዲከተብና ከ12 ዓመት በላይ የሆኑትን ልጆቹንም እንዲያስከትብ ዶ/ር ዮሃንስ ጥሪ አቅርበዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *