መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 6፤2014-ደብረ ብርሀን ከተማ ከ72 በላይ ፀጉረ ልውጦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ደብረ ብርሀን ከተማ ከ72 በላይ ፀጉረ ልውጦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በደብረ ብርሀን ከተማ ከ72 በላይ ፀጉረ ልውጦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማዋ ሰላም እና ደህንነት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ዳንኤል እሸቴ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በአሁኑ ሰዓት በከተማው ላይ ያሉ የፀጥታ መዋቅሩ በማዘጋጀት እና ማህበረሰቡን የማንቃት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልፆል፡፡በከተማዉ ፀጉረ ልውጦችን የመያዝ ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ እና በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ዳንኤል ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናረዋል፡፡

በሌላ በኩል የተፈናቃዮች ቁጥር በየእለቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩ ተመልክቷል፡፡የከተማዋ የፀጥታ ሁኔታ በከፊል እንደተስተካከል የገለፁት ሀላፊው ተፈናቃዮች አሁንም ድጋፍ እየደሚያስፈልጋቸው በማወቅ የከተማው ማህበረሰብ፣ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ እንዲያደርጉ አቶ ዳንኤል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *