መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 7፣2014-በዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ ሶስት ሰዎች ተገደሉ ❗️

በዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ ሶስት ሰዎች ተገደሉ ❗️

በዛሬዉ እለት በዩጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ ሁለት ኃይለኛ ፍንዳታዎች መድረሳቸዉን ተከትሎ ፖሊስ ጥቃት መሰንዘሩን ይፋ አድርጓል፡፡ሁለቱም ፍንዳታዎች የተከሰቱት በማዕከላዊ የንግድ አውራጃ ውስጥ ሲሆን አንደኛው በማዕከላዊ ፖሊስ ጣቢያ አቅራቢያ እና ሁለተኛው በሀገሪቱ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት መወሰወኛ ፓርላማ መግቢያ አጠገብ እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

የዩጋንዳ ጤና ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢማኑኤል አይኔቢዮና በትዊተር ገፃቸው እንዳሰፈሩት ከሆነ በኡጋንዳ ዋና ከተማ ካምፓላ በተፈጸመ መንትያ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃቶች ቢያንስ 3 ሰዎች ሲገደሉ 33 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸዉን ይፋ አድርገዋ፤፡፡የዩጋንዳ ፖሊስ ረዳት ኢንስፔክተር ጄኔራል ኤድዋርድ ኦቾም ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደተናገሩት ክስተቱ ጥቃት ነበር ማለት እንችላለን ነገር ግን ተጠያቂው ማነዉ የሚለዉን በምርመራ የሚደረስበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

አንድ አጥፍቶ ጠፊ በፖሊስ ጣቢያ የፍተሻ ኬላ አካባቢ የመጀመሪያውን ፍንዳታ ያደረሰ ሲሆን፥ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የፖሊስ ቃል አቀባይ ፍሬድ ኢናንጋ ተናግረዋል። በሞተር ሳይክል የመጡ ሁለት አጥፍቶ ጠፊዎች ያፈነዱት ቦንብን ተከትሎ አንድ ሌላ ሰው ህይወቱ አልፏል፡፡

የጸጥታ መኮንኖች ፍንዳታወቹ በተፈጸመባቸው አካባቢዎች ማስረጃ ለመፈለግ አነፍናፊ ውሻዎችን አሰማርተዋል፡፡ለፍንዳታው ሃላፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም ባለፈው ወር አይኤስ የሽብር ቡድን ኃላፊነቱን በወሰደበት ፍንዳታ ሁለት ሰዎች መገደላቸዉ ይታወሳል፡፡በተጨማሪም ባለፈው ወር አንድ አጥፍቶ ጠፊ በአውቶብስ ላይ ቦንብ በማፈንዳት ራሱን ገድሎ ሌሎችን ማቁሰሉን የዩጋንዳ ፖሊስ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *