መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 7፣2014-ናይጄሪያዊ ተማሪ የዩኒቨርሲቲ መምህርን ራሷን እስክትስት በመደብደቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ❗️

ናይጄሪያዊ ተማሪ የዩኒቨርሲቲ መምህርን ራሷን እስክትስት በመደብደቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ❗️

በናይጄሪያ የሚገኘው የኢሎሪን ዩኒቨርሲቲ ተማሪ አንዲት ሴት መምህርን ደብድቧል በሚል ክስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዉሏል፡፡ተማሪው በመጨረሻ ዓመት የፕሮጀክት ስራ ላይ አለመግባባት መፈጠሩን ተከትሎ ወደ ተቆጣጣሪዋ መምህር ማምራቱን ፖሊስ አስታዉቋል።

በደረሰባት ጥቃት ጭንቅላቷ ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ መምህሯ በኮማ ውስጥ መግባቷ ተሰምቷል፡፡ተማሪው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሲሆን መምህሯ ስሙ ለጊዜዉ ባልተጠቀሰሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት ይገኛል፡፡

የዩንቨርስቲው ቃል አቀባይ ኩንሌ አጎጉን ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ድርጊቱ መፈጸሙን አረጋግጠዋል፡፡መምህሯ በማገገም ሂደት ላይ እንደምትገኝም የዩኒቨርሲቲዉ ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *