መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 7፣2014-የህንድ ፍርድ ቤት በኒዉ ዴሊህ ከተማ በአየር ብክለት የተነሳ ሰራተኞች ከቤት ውስጥ ሆነዉ እንዲሰሩ አዘዘ

የህንድ ፍርድ ቤት በኒዉ ዴሊህ ከተማ በአየር ብክለት የተነሳ ሰራተኞች ከቤት ውስጥ ሆነዉ እንዲሰሩ አዘዘ

የህንድ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለሀገሪቱ ባለስልጣናት ባሳለፈዉ ዉሳኔ በኒዉ ዴሊህ እና በአቅራቢያው ባሉ ከተሞች ውስጥ ቢሮዎች፣ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ በማድረግ ሚሊዮኖች ከቤት ዉስጥ እንዲሠሩ መወሰኑን ይፋ አድርጓል፡፡ከህዳር ወር ጀምሮ መርዛማ ጭጋጋማ የአየር ንብረት በኒው ዴሊ መመዝገቡን ተከትሎ የከተማዋ ባለስልጣናት ቅዳሜ እለት የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎችን ወስደዋል፡፡

በዚህም መሰረት ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ እና የግንባታ ስራዎችን ለአራት ቀናት እንዲቆሙ የወሰኑ ሲሆን የህንድ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደግሞ ይህንን ትዕዛዝ በትላንትናዉ እለት አሳልፏል፡፡በከተማዋ ነዋሪዎች የቀረበውን አቤቱታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የሶስት ዳኞች ቡድን መሪ የሆኑት ዋና ዳኛ ኤንቪ ራማና ሰራተኞች ከቤት ውስጥ ሥራ እንዲሰሩ ትዕዛዝ እንመራለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የአየር ጥራት መረጃ ጠቋሚ በትላንትናዉ ዕለት በኒዉ ዴሊህ ውስጥ ከ500 ደረጃ በ343 ላይ የሚያሳይ የነበረ ሲሆን ፣ ይህ ምልክት ለረጅም ጊዜ በሰዎች ላይ የመተንፈሻ አካላት ህመም ሊያስከትል የሚችል እንደሆነም ተጠቁሟል። በዋና ከተማዋ ኒዉ ዴሊህ ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ላይ የሙቀት መጠኑ ቢቀንስም በከተማዋ በተካሄደው የሂንዱ ዲዋሊ ፌስቲቫል ምክንያት የአየር ጥራት ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ ተዳክሟል፡፡

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አስፈላጊ ያልሆኑ የተሽከርካሪ ፍሰትን ለማስቆም፣ የኢንዱስትሪ ብክለትን ለመቀነስ የሚያስችል እርምጃዎችን አዟል።በአለም ላይ እጅግ የተበከለች ዋና ከተማ በሆነችው በዴሊህ ውስጥ ለደካማ የአየር ጥራት ምክንያቱ ከከተማው ውጭ በከሰል የሚመረቱ እፅዋት እንዲሁም ቆሻሻን በአደባባይ ማቃጠል ይገኙበታል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *