መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 7፣2014-ጆ ባይደን እና ዢ ጂንፒንግ ለመጀመሪያ ጊዜ የቨርቿል ውይይት አደረጉ

ጆ ባይደን እና ዢ ጂንፒንግ ለመጀመሪያ ጊዜ የቨርቿል ውይይት አደረጉ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና የቻይናው አቻቸው ዢ ጂንፒንግ የመጀመሪያውን ፊት-ለፊት የቨርቿል ጉባኤ አድርገዋል። በጉጉት የተጠበቀው ይህ ስብሰባ የአለማችን ሁለቱ ታላላቅ የኢኮኖሚ ባለቤት ሀገራት መካከል እንደ ታይዋን፣ ንግድ እና የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ግንኙነታቸው ላይ ውጥረቱ እየጨመረ ባለበት ጊዜ ነው።

ባይደን እንደተናገሩት ሁለቱም ሀገራት ፉክክራቸው ወደ ግልፅ ግጭት ውስጥ እንዳይገባ የማድረግ ሃላፊነት አለባቸው ብለዋል ።ባይደን ወደ ዋይት ሀውስ ከገቡ በኋላ ሁለቱም መሪዎች ያደረጉት ጠቃሚ ውይይት እንደሆነም ተነግሯል።

ሁለቱም መሪዎች ሞቅ ያለ ሰላምታ የተለዋወጡ ሲሆን ዢ የቀድሞ ወዳጄን ባይደንን በማየቴ ደስተኛ ሆኛለው ሲሉ ተናግረዋል።ዢ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነትን ማሻሻል እና በአንድነት ፈተናዎችን መጋፈጥ አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል።

እንደ የአየር ንብረት ለውጥ እና ኮቪድ-19 ያሉ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶችን ለመጋፈጥ ጤናማ የቻይና እና የአሜሪካ ግንኙነት እንደሚያስፈልግ የቻይና መንግስት ሚዲያ ገልጿል። ተፎካካሪ ሀገራቱ ባለፈው ሳምንት በግላስጎው ስኮትላንድ በተደረገው ጉባኤ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቅረፍ የጋራ መግለጫ በማውጣት በርካቶችን ማስገረማቸው ይታወሳል።

የሰው ልጅ በአለምአቀፍ መንደር ውስጥ ይኖራል በርካታ ፈተናዎችን በጋራ እንጋፈጣለን ስለዚህም የቻይና እና አሜሪካ ግንኙነትና ትብብርን ማሳደግ አለብን ሲሉ ዢ ተናግረዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *