መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 8፤2014-በጋምቤላ ክልል ራሱን የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ብሎ ከሚጠራው ኃይል ታጣቂዎች ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ አንድ ታጣቂ ሲገደል ሀያ አራት ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ሰጡ

ለአሸባሪው ሸኔና ህወሐት ተላላኪ በሆነው ጋነግ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ በመታለል ከቡድኑ ጋር ተቀላቅለው የነበሩ ሰዎች የቡድኑ ዓላማ አገር ማፍረስ መሆኑን በመገንዘብ በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ሰጥተዋል ሲሉ የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያ ጽህፈት ቤት ዋና ሃላፊ አቶ ኦግቱ አዲንግ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ቡድኑ ከአሸባሪው ህወሃትና ሸኔ ጋር አገር የማፍረስ ሴራ ነድፎ በመንቀሳቀሱ እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በተደረገ ውይይት ወጣቶቹ በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን መስጠታቸውን ተናግረዋል።ጫካ ገብተው የነበሩ ታጣቂዎች ከልዩ ሃይሉ ጋር ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ የአንድ ታጣቂ ህይወት ሲያልፍ ሀያ አራት ታጣቂዎች ደግሞ በተደረገላቸው ዳግመኛ ጥሪ እጃቸውን ሰጥተዋል፡፡

ቀሪ ያልተመለሱ የጋነግ አባላትም የመረጡት አማራጭ ስህተት እንደሆነ አውቀው በሠላማዊ መንገድ በመምጣት በክልሉ ውስጥ በሚደረገው የሠላም እና የልማት እንቅስቃሴ ሚናቸውን መጫወት እንደሚኖርባቸዉ ጥሪ ቀርቧል፡፡በጫካ የነበሩ የሽፍታው ቡድን አባላት በሠላማዊ መንገድ እንዲገቡ በርካታ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱ ተልጿል።

ወደ ክልሉ የሰላም ጥሪ ተቀብለው የተመለሱ የቡድኑ ታጣቂዎች በበኩላቸው መንግስት ያስተላለፈላቸወ የሰላም ጥሪ ተቀብለው ሲመጡ በተደረገላቸው አቀባበል መደሰታቸውን ተናግረዋል።ከትጥቅ ትግል ይልቅ ሠላማዊ መንገድ መከተል ለሁሉም አስፈላጊ መሆኑን አቶ ኦግቱ አዲንግ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ቤቴልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *