መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 8፤2014-የአሜሪካ ዲፕሎማት በሱዳን በቁም እስር ላይ ከሚገኙት አብደላ ሃምዶክ ጋረ መወያየታቸው ተሰማ

የአሜሪካ ዲፕሎማት በሱዳን በቁም እስር ላይ ከሚገኙት አብደላ ሃምዶክ ጋረ መወያየታቸው ተሰማ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ፅህፈት ቤት የአፍሪካ ረዳት ፀሀፊ በሱዳን ለሶስት ቀናት ባደረጉት ጉብኝት ካለፈው ወር መፈንቅለ መንግስት ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኙትን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክን አነጋግረዋል።

ዩዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ረዳት ፀሀፊ ሞሊ ፒ የሱዳንን ዲሞክራሲያዊ ሽግግር ወደነበረበት መመለስ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መወያየታቸውን በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።ረዳት ፀሀፊዋ የመፈንቅለ መንግስቱ መሪ አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ማግኘታቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

አሜሪካ በሱዳን የተደረገው የመንግስት ግልበጣ በማውገዝ የሲቪልና ወታደራዊው ጥምረት ወደ ስልጣን እንዲመለስ ግፊት ማድረጓን ቀጥላለች።የረጅም አመታት የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ከስልጣን መውረድን ተከትሎ የሽግግር መንግስቱ ለምርጫ መንገዱን ይጠርጋል የሚል ተስፋ ተጥሎበት ነበር።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *