መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 9፤2014-አሜሪካ የሃይማኖት ነፃነትን ይጋፋሉ ብላ ካሰፈረቻቸው ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ናይጄሪያ አስወጣች

አሜሪካ የሃይማኖት ነፃነትን ይጋፋሉ ብላ ካሰፈረቻቸው ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ናይጄሪያ አስወጣች

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ወደ አገሪቱ ከሚየደርጉት ጉብኝት አስቀድመው ናይጄሪያን የሃይማኖት ነፃነትን ከሚጋፉ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ አውጥታለች። የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ባለፈው አመት ናይጄሪያን በሃይማኖታዊ ነፃነት ላይ ከፍተኛ ጥሰት ከሚፈፅሙ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ አስቀምጧል።

በ2021 ምያንማር፣ ቻይና፣ ኤርትራ፣ ኢራን፣ ሰሜን ኮሪያ፣ ፓኪስታን፣ ሩሲያ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ታጂኪስታን እና ቱርክሜኒስታን ባሉበት ዝርዝር ውስጥ ናይጄሪያ መካተቷ ይታወሳል። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ፅህፈት ቤት መረጃ እንደሚያሳየወ አልጄሪያ፣ ኮሞሮስ፣ ኩባ እና ኒካራጓ የሃይማኖት ነፃነትን በጣሱ መንግስታት ልዩ ዝርዝር ውስጥ ይገኛሉ።

ሆኖም በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱት ቦኮ ሃራም እና ኢስዋፕ የተባሉት የሽብር ቡድኖች አሁንም በሀገሪቱ ስጋት ደቅነው ይገኛል።ብሊንከን ኬንያን እና ሴኔጋልን ባካተተው የሶስት ሀገራት ጉዟቸው ሁለተኛ ዙር በዛሬው እለት ናይጄሪያን እየጎበኙ ይገኛል።

ፕሬዝዳንቱ ከናይጄሪያው ፕሬዝዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ጋር በመገናኘት ሁለቱ ሀገራት በአለም አቀፍ ጤና፣ ደህንነት፣ የሃይል አቅርቦት በማስፋፋይ እና በኢኮኖሚ እድገት ላይ እንዴት የበለጠ ትብብር ማድረግ እንደሚችሉ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል። ናይጄሪያ ለጸጥታና መረጋጋት ስጋት ከሆኑ አካላት ጋር እየተዋጋች ትገኛለች።

ከነዚህም ውስጥ ለረጅም ጊዜ ሲካሄድ የቆየው የቦኮ ሃራም አማጽያን ጥቃት፣ በማህበረሰብ መካከል ያለው የእርስ በእርስ ግጭት እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በታጠቁ ቡድኖች በትምህርት ቤቶች የሚካሄደው የጅምላ አፈናና እገታ መጨመር ስጋት ደቅኗል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *