መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 9፤2014-እኛ ላይ ጫና የሚፈጥሩ የውጭ ሀገራት የፈበረኩት የጦር መሳሪያን መጣያ በማጣታቸው ነው ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ❗️

እኛ ላይ ጫና የሚፈጥሩ የውጭ ሀገራት የፈበረኩት የጦር መሳሪያን መጣያ በማጣታቸው ነው ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ❗️

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃለ አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዛሬው እለት ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫው በፖለቲካ፣በዲፕሎማሲ በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲና በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ረገድ ማብራሪያን ሰጥተዋል።

በዋናነትም ከተነሱ ጉዳዮች መካካከል የተመድ ሰራተኞች ጋር ያለው ጉዳይ በተመለከተ ህገወጥ በመሆናቸው እና ህግ በመጣሳቸው ህጋዊ እርምጃ የተወሰደባቸው መሆኑንና በሌሎች መተካት ትችላላችሁ ብለናል ሆኖም እስካሁን አልተኩም ሲሉም አምባሳደር ዲና መናገራቸውን ብስራት ሬድዮ ሰምቷል።

ኢትዮጲያ ላይ ጫና እየፈጠሩ ያሉት ሀገራት ጦርነት እዚህ ከሌለ የጦር መሳሪያዎቻቸውን የሚሸጡበት ያጣሉ፤ ለዚህም ነው ሀሰተኛ ወሬ የሚነዙት ድርጊታቸው ወደ አፍሪካ የጦር መሳሪያ ለመላክ ሲባል የተጠነሰሰ ነው ያመረቱትን መጣያ በማጣታቸው የሚሰሩት ስራ ነው ሲሉ ተናግረዋል ።

የአፍሪካን ጉዳይ ለአፍሪካ ተው የሚለውን ግፊት እያደርግን የአፍሪካን ችግር በአፍሪካ እንፈታለን፤ ይህንንም ስንል የአፍሪካን ድጋፍ እንሻለን ሌሎች የኢትዮጵያ አጋሮች ይሄንን በማድረግ ማገዝ አለባቸው ሲሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ጨምረው ተናግረዋል።

ቤተልሄም እሽቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *