መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 10፤2014-በኢትዮጵያ 18 በመቶ የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል ብቻ በአግባቡ በተሰሩ መጸዳጃ ቤቶች ይጠቀማል ተባለ

እንደ የዓለም ጤና ድርጀት እና ዩኒሴፍ መረጃ በኢትዮጵያ 83 በመቶ የሚሆነው የህብረተሰብ ክፍል የመፀዳጃ ቤት ይጠቀማል ቢባልም ፤ የዓለም ጤና ድርጅት የሚጠይቀውን መስፈርት ባሟለ መልኩ በአግባቡ በተሰሩ መጸዳጃ ቤቶች የሚጠቀሙት 18 በመቶ ብቻ ስለመሆናቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ቀሪው 65 በመቶው አመቺ ባልሆነ ፣ ባልተሻሻለ እና የዓለም ጤና ድርጅት የሚጠይቀውን መስፈርት ባላሟላ መልኩ የሚጠቀሙ ስለመሆናቸው ፤ የጤና ሚኒስቴር ሀይጂን እና አካባቢ ጤና አጠባበቅ ረዳት ዳሬክተር አቶ አሽረፈዲን ዩያ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ 17 በመቶ የሚሆኑት ከነአካቴው የመጸዳጃ ቤት እንደማይጠቀሙ ማለትም በየአካባቢው እንደሚፀዳዱ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መረጃ ያሣያል፡፡

እንደ አቶ አሸርፈዲን ማብራሪያ ኢትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ስርጭት በስፋት የሚታዩባት ስትሆን ፤ ይህንኑ ችግር ለመፍታት በየዓመቱ ከፍተኛ ገንዘብ አንደምታወጣ ተናግረዋል፡፡ ይህንኑ ለማስቀረት ህብረተሰቡ መጸዳጃ ቤቶችን ሲገነባ እና ሲጠቀም በትኩረት ሊሆን እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

ዛሬ ዓለም አቀፉ የመጸዳጃ ቤት ቀን ነዉ፡፡

ትዕግሰት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *