መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 10፤2014-ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ለካማላ ሀሪስ በጊዜያዊነት በዛሬው እለት ያስተላልፋሉ

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዓመታዊ የጤና ምርመራቸውን ሲያካሂዱ በሰመመን ስለሚቆዩ ለጊዜው ስልጣናቸውን ለካማላ ሀሪስ የሚያስተላልፉ ይሆናል። ካማላ ሀሪስ የፕሬዝዳንትነት ስልጣን የተሰጣቸው የመጀመሪያዋ ሴት በታሪክ ያደርጋቸዋል።

የሕክምና ምርመራውን ባይደን በ79ኛ ዓመት የልደታቸው ዋዜማ ላይ ያደርጋሉ።ሃሪስ የአሜሪካን ጦር እና የኒውክሌር ጦር መሳሪያን ለጊዜው ይቆጣጠራሉ።

የዋይት ሀውስ ፕሬስ ሴክሬታሪ ጄን ፓሳኪ በሰጡት መግለጫ ምክትል ፕሬዚዳንቷ በምዕራባዊ ዊንግ ቢሮዋቸው ውስጥ ስራቸውን ይቀጥላሉ ብለዋል ። የ57 ዓመቷ ሃሪስ የመጀመሪያዋ ሴት የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *