መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 13፤2014-በሜኤሶ ከተማ ወድቆ በተገኘ ቦምብ ሲጫወቱ የነበሩ የሁለት ህጻናት ህይወት አለፈ❗️

በሜኤሶ ከተማ ወድቆ በተገኘ ቦምብ ሲጫወቱ የነበሩ የሁለት ህጻናት ህይወት አለፈ❗️

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሀረርጌ ዞን ሚኤሶ ከተማ ወድቆ የተገኘ ቦንብን ሲቀጠቅጡና ሲጫወቱ ከነበሩ ስድስት ህጻናት መካከል የሁለቱ ህይወት ማለፉን የከተማው ፖሊስ አስታወቋል፡፡

የሜኤሶ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ምክትል ዳይሬክተር አህመዲን ከድር በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት ህዳር 9 ቀን 2014 ዓ.ም በሚኤሶ ከተማ ልዩ ቦታው ካኪ ሰፈር በተባለ አካባቢ የቦምቡ ፍንዳታው ተከስቷል።

በወቅቱ በጨዋታ የነበሩ 6 ህጻናት ወድቆ ያገኙትን ቦንብ ሲቀጠቅጡ በመፈንዳቱ የተነሳ የሁለቱ ህጻናት ህይወት ሲያልፍ፥ በሶስት ህጻናት ላይ ከባድ፥ በአንዱ ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።

ህይወታቸው ያጡት ሁለቱ ህጻናት የ11 አመት ታዳጊዎች ሲሆኑ፥ ጉዳት የደረሰባቸው ደግሞ ከ5 እስከ 13 ዓመት የእድሜ ክልል ላይ የሚገኙ መሆናቸውን ሳጅን አህመዲን ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *