መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 13፤2014-በአዲስ አበባ 40 ደቂቃ በፈጀ የነፍስ አድን ስራ ከባቡር አደጋ የአንድን ሰው ህይወት ማትረፍ ተቻለ❗️

በትላንትናው እለት ምሽት 2 ሰዓት 50 ደቂቃ በአዲስ አበባ ሪቼ የባቡር ጣቢያ ወይም መስከረም ማዞሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የባቡር አደጋ የደረሰበት ግለሰብን ህይወት ለማትረፍ 40 ደቂቃ የጠየቀ የነፍስ አድን ስራ በማከናወን ተጎጂውን ማትረፍ መቻሉን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ድርጅት አስታውቋል፡፡

ህዳር 12 ቀን 2014 ዓ.ም ምሽት 2 ሰዓት 50 አካባቢ ከቃሊቲ ወደ ፒያሳ በሚጓዘው ባቡር አደጋው መድረሱን የድርጅቱ የጥንቃቄ እና ደህንነት አገልግሎት ክፍል ሀላፊ ወይዘሮ ሳምራዊት አቡበክር ለብስራት ሬድዮ ተናግተዋል።አደጋው የደረሰበት ግለሰብ እድሜ ባይገለፅም በጉልምስና የእድሜ ክልል የሚገኝ ሲሆን በአካባቢው ከሚገኘ የፀጥታ አካላት በተገኘ መረጃ መሰረት ግለሰቡ መጠጥ ጠጥቶ በስካር ውስጥ ሆኖ አደጋው ደርሶበታል።

ከአደጋው በኃላ የፀጥታ አካላት እና የአዲስ አበባ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ ስራ አመራር ሰራተኞች ደርሰው 40 ደቂቃ በፈጀ የነፍስ አድን ስራ ህይወቱን ማትረፍ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡ግለሰቡ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶበት በዘውዲቱ ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛል፡፡

የባቡር ግጭት አደጋ ከሌሎች የተሸከርካሪ አደጋ አይነቶች የሚለይ በመሆኑ እግረኞች የባቡር መተላለፊያ መስመሮችን ወይንም መሻገሪያዎችን ሲያቋርጡ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሀላፊዋ ወይዘሮ ሳምራዊት ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

ህዳር 14፤2014- በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *