መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 14፣2014-ታሊባን በቴሌቪዥን ድራማ ላይ ሴቶች እንዳይተወኑ የሚያደርግ አዲስ ህግ ይፋ አደረገ

የአፍጋኒስታን መንግስት ታሊባን ባወጣው አዲስ ህግ መሰረት ሴቶች በሀገሪቱ በሚገኙ የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ እንዳይታዩ ከልክሏል።ሴት ጋዜጠኞችንና አቅራቢዎችን ህጉ ባይከለክልም ተሸፍነው መቅረብ እንዳለባቸው ያዛል።

አዲስ የወጣው ደንብ ግልፅ ያልሆነ እና ለትርጓሜ የተጋለጠ ነው የሚል ሀሳብ እየተሰጠበት ይገኛል።ታሊባን በነሀሴ ወር የተቀዳጀውን ድል ተከትሎ ቀስ በቀስ ጥብቅ ገደቦች ተግባራዊ እንዲደረጉ መመሪያ እያወጣ ይገኛል።

ቡድኑ ስልጣን እንደተረከበ ሴቶች ወደ ትምህርት ቤቶች እንዳይሄዱ ከልክሏል።የአፍጋኒስታን የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የሚያሳዩይ በአብዛኛው የውጪ ሀገራት ድራማዎች ሲሆኑ መሪ ሴት ገፀ ባህሪ ያላቸው ናቸው።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *