መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 14፤2014-የካሾግጂ እጮኛ ጀስቲን ቢበር በሳዑዲ አረቢያ ሊያካሄድ እቅድ የተያዘለትን የሙዚቃ ድግስ እንዲሰርዝ ጠየቀች

በግፍ የተገደለው ጋዜጠኛ ጀማል ካሾግጂ እጮኛ በቀጣዩ ወር ድምፃዊው ጀስቲን ቢበር በሳዑዲ አረቢያ ሊያደርገው እቅድ የተያዘለትን የሙዚቃ ኮንሰርት እንዲሰርዝ ጠይቃለች።ካናዳዊው ድምፃዊ በጅዳ በሚካሄደው የፎርሙላ ዋን ግራንድ ፕሪ ላይ እንዲያቀነቅን ከተመረጡት መካከል አንዱ ነው።

የካሺግጂ እጮኛ ሀቲስ ሴንጊዝ በፃፈችው ግልፅ ደብዳቤ ቢበር የሙዚቃ ድግሱን እንዲሰርዝ ጠይቃለች።የሳዑዲ አረቢያ መንግስትን በመተቸት የሚታወቀው ጋዜጠኛ በ2018 በቱርክ ኢስታንቡል በሚገኘው የሳዑዲ ቆንስላ ፅህፈት ቤት ውስጥ በግፍ መገደሉ ይታወሳል።

ካሾግጂ ወደ ቆንስላው የገባው ለጋብቻቸው ስነድ ለመውሰድ እንደነበር ይታወሳል።ፅህፈት ቤቱ በራፍ ላይ ካሾግጂ እስኪወጣ ስትጠብቅ የነበረችው ሴንጊዝ በዛው ቀረ።አስክሬኑም ከፅህፈት ቤቱ ተቆራርጦ እንዲወጣ መደረጉ አይዘነጋም።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ቢበርን ጨምሮ ሌሎች አርቲስቶች በዚህ ኮንሰርት ላይ ስራቸውን እንዳያቀርቡ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *