
አሜሪካ እውነታውን መቀበል እና የጣለችዉን ማዕቀቡን ማንሳት አለባት ሲሉ የኢራን ተደራዳሪ ተናገሩ
በሚቀጥለው ሳምንት በቪየና በሚደረገው የኒውክሌር ድርድር ዩናይትድ ስቴትስ እውነታውን መቀበል እና በኢራን ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ለማንሳት መስማማት አለባትሲሉ የቴህራን ከፍተኛ ተደራዳሪ ተናግረዋል፡፡የኢራን ተወካዮች እና ሌሎች የ 2015 የኒውክሌር ስምምነት ፈራሚዎች አሜሪካ በ2018 ጥላዉ ከወጣችበት የጋራ የድርጊት መርሃ ግብር ለመመለስ በቀጣዩ ሳምንት በኦስትሪያ ይመክራሉ፡፡
ቻይና፣ ሩሲያ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ፈረንሳይ ፣ጀርመን እና የኢራን አዲሱ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ አስተዳደራቸውን እንዲመሰርቱ በሚል በሰኔ ወር የቆመዉ ስድስት ዙር ንግግር ይቀጥላል፡፡ከተሳካ ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ የጣለችው ከባድ ማዕቀብ እንዲነሳ እና ኢራንን የስምምነቱ ውል ሙሉ በሙሉ ወደ ማክበር በሚደረገው ድርድር ላይ በተዘዋዋሪ ትሳተፋለች።
ኢራን ቀደም ሲል በቪየና ውስጥ ጥሩ ስምምነት ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን መናገሯ የሚታወስ ሲሆን ነገር ግን አሜሪካ የ2018ቱን ከድርጊት መርህ የመሻር ሃላፊነት መቀበል አለባት ፣ ከ2018 ጀምሮ የተጣለውን ማዕቀብ በአንድ ጊዜ ማንሳት እና ስምምነቱን እንደገና እንደማትወጣ ዋስትና መስጠት ይኖርባታል ስትል ቴህራን አስታዉቃለች፡፡
በሚኪያስ ጸጋዬ