መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 14፤2014-የተሸከርካሪ ሰሌዳ መሰጠት ቢቆምም በደላሎች በኩል ሽያጭ እየተከናወነ ይገኛል የሚለዉ ቅሬታ እንዳልደረሰዉ የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባላስልጣን አስታወቀ

የተሸከርካሪ ሰሌዳ መሰጠት ቢቆምም በደላሎች በኩል ሽያጭ እየተከናወነ ይገኛል የሚለዉ ቅሬታ እንዳልደረሰዉ የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባላስልጣን አስታወቀ

የተለያዩ የተሸከርካሪ ባለቤቶችች በተደጋጋሚ ሰሌዳ እንዲሰጠን ብንጠይቅም ልናገኝ አልቻልንም ነገር ግን በደላሎች ከ10 እስከ 30 ሺህ ድረስ ብር ከከፈልን ሊሰጥ እንደሚችሉ እየነገሩን ነው ሲሉ የተሸከርካሪ ባለቤቶች ለብሰራት ሬዲዮ ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባላስልጣን መስሪያ ቤት ስለጉዳዩ ብስራት ሬድዮ ባቀረበዉ ጥያቄ ባላፈው አንድ ወር የሰሌዳ ምርት ባለመኖሩ የሰሌዳ አገልግሎት እየተሰጠ አለመሆኑን የባለስልጣኑ የተሸከርካሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ዘለቀ ተናግረዋል፡፡

እየቀረበ ያለውን ቅሬታ በተመለከተም ክፍያ እየተጠየቅን ነው የሚል አካል እስካሁን እንዳልመጣ የተናገሩት ሃላፊው ሆኖም የተሸከርካሪ ሰሌዳ አላገኘንም የሚለው ቅሬታ ግን ልክ ነው እንደሃገር የተሸከርካሪ ሰሌዳ ባለመኖሩ የተነሳ ነው ብለዋል፡፡ የተሸከርካሪ ሰሌዳ ምርት ሊቆም የቻለው የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ህጋዊ ሰውነቱን በማጣቱ ምክንያት እና ሰሌዳ የማምረት ውክልና ለፐብሊክ ሰርቪሰ ትራንስፖርት ክፍል በመሰጠቱ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

አሁን ከፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ጋር ውል ለማሰር በሂደት ላይ መሆናቸውን የተናገሩት ሃላፊው ውል የመፈጸም ሂደቱ በሁለት ቀናት ውስጥ ከተጠናቀቀ በተያዘዉ ሳምንት መጨረሻ ሰሌዳ ለተገልጋዪች ለማቅርብ እየተሰራ መሆኑን አቶ ዳዊት ዘለቀ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ቤተልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *