መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 14፣2014-በደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኙ ተፈናቃዮች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ በመጨመሩ የመጠለያ ጣቢያዎች ቁጥር ወደ ዘጠኝ ከፍ ተደረገ

ሽብርተኛዉ ህወኃት የከፈተዉን ጥቃት ተከትሎ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደብረ ብርሀን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከዚህ ቀደም ስድስት የመጠለያ ጣቢያዎች የተዘጋጀ ሲሆን የተፈናቃዮች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ የተነሳ ቁጥሩ ወደ ዘጠኝ ከፍ እንዲል መደረጉ ተገልጿል፡፡

ከዚህ ቀደም የተፈናቃዮች ቁጥር 145 ሺ እንደሚጠጋ ለብስራት ሬድዮ የገለጹት የደብረ ብርሃን ከተማ ሰላም እና ደህንነት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ዳንኤል እሸቴ በአሁኑ ሰአት ደግሞ በከፍተኛ ደረጃ የተፈናቃዮች ቁጥር መጨመሩን ተናግረዋል፡፡እንዲሁም ለተፈናቃዮቹ የጤና እንክብካቤ እንዲያገኙ እየተደረገ ሲሆን ለዚህ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከጤና አኳያ የተለያዩ ስራዎች እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በመጠለያ ጣቢያ የሚነሱ የተለያዩ ችግሮች ለመቅረፍ እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡የከተማውን የጸጥታ ሁኔታ በተመለከተ ከ3ሺ በላይ ወጣቶች ተደራጅተው የከተማውን የጸጥታ ሁኔታ የማረጋጋት እና ጸጉረ ልውጦች የመለየት ስራ እየሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *