መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 16፤2014-በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ የተሽከርካሪ ሰሌዳ መሰጠት ሊጀመር ነው ❗️

በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ የተሽከርካሪ ሰሌዳ መሰጠት ሊጀመር ነው ❗️

የተሸከርካሪ ሰሌዳ አላገኘንም የሚለው የተሽከርካሪ ባለቤቶች ቅሬታ ለብስራት ሬዲዮ መምጣቱን ተከትሎ እንደሃገር የተሸከርካሪ ሰሌዳ ባለመኖሩ የተነሳ ችግሩ እንዳጋጠመ የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባላስልጣን ማስታወቁ ይታወሳል::

በተለይ ቅሬታ አቅራቢዎች ለሰሌዳ በደላሎች አማካይነት ከ10 እስከ 30 ሺህ ብር እንደሚጠየቁ መናገራቸውን ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ አይዘነጋም።ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ይህ ቅሬታ እንዳልደረሰው ገልጿል።

አሁን ላይ ችግሩ በመቅረፉ ከነገ ጀምሮ ሰሌዳ መሰጠት እንደሚጀምር የባለስልጣኑ የተሸከርካሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ዘለቀ በተለይ ለብስራት ሬዲዪ ተናግረዋል፡፡

አሁን ባለው ሁኔታ ለአዲስ አበባ የአሸከርካሪ ባለቤቶች ለማዳረስ የሚያስችል በቂ ሰሌዳ ለቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መከፋፈሉን አንስተው ከኢት ሰሌዳ ውጪ ማንኛውም ተገልጋይ የሚፈልገውን ሰሌዳ ማግኘት ይችላል ብለዋል

ከምርቱ በአግባቡ በመጀመሩ እንደከዚህ ቀደሙ አይነት ችግር እንደማይፈጠር አቶ ዳዊት ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል

ቤተልሄም እሸቱ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *