መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 16፤2014-በደብረ ማርቆስ ከተማ ከ270 በላይ ፀጉረ ልውጦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በደብረ ማርቆስ ከተማ ከ270 በላይ ፀጉረ ልውጦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በከተማው 276 ፀጉረ ልውጦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን በደብረማርቆስ ከተማ ዞን ፖሊስ መምሪያ የመረጃ ክትትል የስራ ሂደት ሀላፊ ኮማንደር መልካሙ አስጨንቅ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በከተማው በተደረገ ጥብቅ ክትትል በ28 ወረዳዎች 148 ወንድ እና 128 ሴት ፀጉረ ልውጦቹ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው የተገለፀው፡፡

በአሁኑ ሰዓት በከተማው ላይ ያሉ የፀጥታ መዋቅር በማዘጋጀት እና ማህበረሰቡን የማንቃት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ እና በከተማዉ ፀጉረ ልውጦችን የመያዝ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ እና በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮማንደር መልካሙ አስጨንቅ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በከተማው ከዚህ ቀደም በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 16 የተለያዩ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦች፣3 ክላሽንኮፕ ጠመንጃ፣ 4 የቃታ መሳሪያዎች ፣ 6 የተለያዪ ካዝናዎች፣1 ገጀራ፣54 የክላሽ ጥይት፣16 የሽጉጥ ጥይቶች እና የተለያዩ የመሳሪያ ወለዋወጫዎች መገኘቱን የሚታወስ ሲሆን በቀጣይም የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው የተገለፀው፡፡

ሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *