
የደብረብርሀን ከተማ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኮ/ር ታዬ ሀብተጊዮርጊስ በቁጥጥር ስር ዋሉ
‘የደህንነት ስጋት ናቸው’ ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉትን ከእስር በመፍታት የተጠረጠሩት የደብረብርሀን ከተማ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ሀላፊ ኮማንደር ታዬ ሀብተጊዮርጊስ በቁጥጥር ስር ዋሉ።
የከተማው ሰላምና ደህንነት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ዳንኤል እሸቴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ የፖሊስ ፅህፈት ቤት ሀላፊው በቁጥጥር ስር የዋሉት ከአሸባሪው ህውሓት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦችን ያለ ኮማንድ ፖስቱ ፈቃድ ከማቆያ እንዲወጡ አድርገዋል በሚል ነው።
በዚህ ወንጀል የተሳተፉ ሌሎች አመራሮች መኖራቸውን በተመለከተም ከህዝብ ጥቆማዎች እየደረሳቸው እንደሚገኝም አቶ ዳንኤል ገልፀው÷ መረጃውን ለማጥራት እየተሠራ ነውም ብለዋል፡፡