
በሱዳን የተካሄደውን ወታደራዊ ስምምነት ውድቅ ለማድረግ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አደባባይ በመውጣት ተቃውሞ አሰምተዋል
በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም እና በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሀገሪቱ ወታደራዊ መሪዎች እየደረሰ ያለውን ጫና የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል።የካርቱም መንትያ ከተማ በምትባለው ኦምዱርማን ወታደራዊ ሀይሎን ለማውገዝ አደባባይ የወጡ ሰልፈኞችን የፀጥታ ሀይሎች አስለቃሽ ጋዝ በመተኮስ በትነዋል።
ሰልፈኞቹ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ከወታደራዊ ሃይሎች ጋር የተደረገውን ስምምነት አውግዘዋል።ታዋቂ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ሃምዶክ ያደረጉትን ስምምነት ክህደት በማለት እያወገዙት ይገኛል።
ስምምነቱ ለመፈንቅለ መንግስት ሂደቱ ፖለቲካዊ ሽፋን መስጠት ነው ሲሉ ሰልፈኞች ተቃውመዋል።
በስምኦን ደረጄ