መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 17፤2014-አንበሳ አውቶቡስ በቀን ከ600ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎችን አጓጉዛለው ሲል አስታወቀ

አንበሳ አውቶቡስ በቀን ከ600ሺ በላይ የሚሆኑ ሰዎችን አጓጉዛለው ሲል አስታወቀ

በአዲስ አበባ ከተማ እና ዙሩያዋ ያለውን የትራንስፖርት ፍላጎት ከሚሸፍኑት መካከል አንዱ የሆነው አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በቀን ከ600ሺ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ባደረገው ጥረት ከአሁን በፊት ከ30 እስከ 25 ደቂቃ ይፈጅ የነበረውን የሰልፍ ቆይታ ጊዜን በማሳጠር ወደ15 ደቂቃ ማውረድ መቻሉን የድርጅቱ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ምስክር ማንደፍሮ ለብስራት ሬድዮ ተናግሩዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ በሰጠው አቅጣጫ መሰረት አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በ125 መደበኛ መስመር፣ በ10 ልዩ መስመሮች እና የታክሲ ሰልፍ በሚታይባቸው በተመረጡ የከተማው ክፍል በቀን በአማካይ 615 አውቶቡሶችን በማሰማራት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

በተጨማሪም በብልሽት የቆሙ ተሽከርካሪዎችን በውስጥ አቅም እና መለዋወጫ ከገበያ ላይ በማፈላለግ ቶሎ ወደ ሥራ ለማስገባት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የነገሩን አቶ ምስክር የድርጅቱ የቴክኒክ ሠራተኞች ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ ኤር ባጎችን በጥገና ክፍሉ መልሶ በመጠገን ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት ተችሏል ብለዋል፡፡

የድርጅቱ ማኔጅመንት አባላትም ተርሚናሎች በመከፋፈል ድጋፍና ክትትል እያደረጉ ይገኛል፡፡በቀጣይ በከተማ አስተዳደሩ በኩል ተጨማሪ አውቶቡሶች ግዢ ተፈጽሞ አገልግሎቱን በስፋት ለማዳረስ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል፡፡

በትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *