መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 17፤2014-የመከላከያ ሰራዊት ካሳጊታን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ!!

የመከላከያ ሰራዊት ካሳጊታን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ!!

የመከላከያ ሰራዊት ከሰሞኑ ባደረገው ፍልሚያ በካሳጊታ የነበረውን የጠላት ኃይል በመደምሰስ ቦታውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ፡፡

ፍልሚያው መቀጠሉንና በዛሬው ዕለትም የወገን ጦር ጭፍራ እና ቡርቃን ለመያዝ ትግሉን ያፋፋመ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

“ካሳጊታን ይዘናል፤ ጭፍራ እና ቡርቃን ዛሬ እንይዛለን” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፡፡

“የምንፈልገው እኛ ሞተን ኢትዮጵያ እንድትቀጥል ማድረግ ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “የኢትዮጵያ ነጻነት አስኪረጋገጥ ወደ ኋላ ማለት የለም” ሲሉ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሰራዊት ሞራል ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው ጠላት ከእኛ ጋር ለመፎካከር የሚያስችል ቁመና የለውም ብለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *