መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 17፤2014-የሰላምና ልማት ማዕከል የተሰኘው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ፈቃድ ተሰረዘ

በቅርቡ አገር ለማፍረስ በድብቅ ሲወያዩ የነበሩትን የእነ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሀቅ፣ እሌኒ ገብረመድህን፣ ብርሀነ ገብረክርስቶስ እና አጋሮቻቸውን ውይይት ያዘጋጀው የሰላም ልማት ማዕከል ፈቃድ መሰረዙን የኢፌዴሪ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን አስታውቋል።

ይህ ማዕከል ሰሞኑን በፕሮፌሰር ኤፍሬም አወያይነት በሽብርተኝነት የተፈረጀው የህወሃት ቡድንን ለመታደግ የቡድኑ አባላትና አንዳንድ ምዕራባውያን የጥቅም አጋሮቹ ዲፕሎማቶች ያካሄዱት ምሥጢራዊ ውይይት አዘጋጅቷል።

ስለሆነም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንቀጽ 4 ንዑስ አንቀጽ 9 መሰረት፤ የሀገርን ህልውናና ሉዓላዊነት እንዲሁም ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ እዝ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ድጋፍ ያደርጋል ተብሎ የሚጠረጠር የሲቪል ማኅበር ድርጅት ፈቃድ እንዲሰረዝ ያዛል በሚለው መሰረት የሰላም ልማት ማዕከል ፈቃድ ተሰርዟል።

የኢፌዴሪ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ባለስልጣኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የማዕከሉ ፈቃድ እንዲሰረዝ በወሰነው በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 አንቀጽ 88/3 መሰረት በኤጀንሲው ዳግም ተመዝግቦ በምዝገባ ሰርተፊኬት ቁጥር 2936 ሕጋዊ እውቅና አግኝቶ እየተንቀሳቀሰ የቆየ መሆኑ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ በአገር ህልውናና ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነን አደጋ ለመከላከል በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንቀፅ 4 ንዑስ አንቀፅ 9 መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ የአገርን ህልውናና ሉዓላዊነት እንዲሁም የሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለቡድኖች የሞራልም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ ያደርጋል ብሎ የሚጠረጥረውን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ፈቃድ እንዲሰረዝ ሊያዝ ይችላል ተብሎ በተደነገገው መሰረት ቀደም ሲል በስም የተጠቀሰው ድርጅት ፈቃድ እንዲሰረዝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ውሳኔ ያሳለፈ መሆኑን የፍትህ ሚኒስቴር በቁጥር ፍ/ሚ-01/ባሰ-9/500773 ሕዳር 17/2014 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ አሳውቋል፡፡

በዚሁም መሰረት የሰላምና ልማት ማዕከል የተባለው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት የምዝገባ የምስክር ወረቀት (ፈቃድ) ከዛሬ ሕዳር 17/2014 ጀምሮ የተሰረዘ መሆኑን አስታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *