መደበኛ ያልሆነ

ህዳር 20፤2014-በምስራቅ ሀረርጌ ዝሆን ገድሎ 1.4 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የዝሆን ጥርስ የሸሸገው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ❗️

በምስራቅ ሀረርጌ ዝሆን ገድሎ 1.4 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የዝሆን ጥርስ የሸሸገው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ❗️

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን አባቢሌ የዱር እንስሳት ፓርክ ውስጥ ዝሆን የገደለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል።በዞኑ ሚዳጋቶላ ቢሉሱማ ቀበሌ ውስጥ ከሚገኘው የአባቢሌ የዱር እንስሳት ፓርክ ውስጥ ሆን ብሎ በህገወጥ መንገድ የጦር መሳሪያ በመያዝ ድርጊቱን ግለሰቡ ፈፅሟል።

ዝሆኑን ከገደለ በኃላ ጥርሱን በመጥረቢያ በመምታት አውልቆ መውሰዱን የሚዳጋቶላ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ምክትል ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ኢብሳ ሌሊሳ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።ተጠርጣሪው የሸሸጋቸው ሁለት የዝሆን ጥርሶች በቁጥጥር ስር ዉለዋል።

የአባቢሌ የዱር እንስሳት ፓርክ ዳይሬክተር አቶ አደም አህመድ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ተጠርጣሪው ሸሽጓቸው የተገኙት የዝሆን ጥርሶች 1.4 ሚሊዮን ብር ሊያወጣ የሚችል እንደነበር ገልፀዋል።ህብረተሰቡ ለዱር እንስሳት የሚደረገውን ጥበቃ እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *