
የሰሜን ኮርያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለሀገሪቱ ዜጎች ስለ ሚሳኤል ሙከራ እና ህዝባቸው ጠንክሮ እንዲሰራ ባስተላለፉት መልዕክት ላይ ሲናገሩ የለበሱት ሌዘር ጃኬት በኮርያ ወጣት ወንዶች ተወዳጅ ሆኗል። ኪም ይህንን የሌዘር ጃኬት ለመጀመሪያ ጊዜ በ2019 ከለበሱ በኃላ የሀገሪቱ ሙሁራንና ፖለቲከኞች ለኪም ያላቸውን ተዓማኝነት ለማሳየት ይህንኑ የቆዳ ጃኬት መልበስ ጀምረዋል።
ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መሪውን ማስመሰል ኪምን የሚያራክስ እና ድፍረት ነው በማለት ሌዘር ጃኬቱን የሚሸጡ ነጋዴዎች ሱቅ እንዲዘጋ ተደርጓል።የሰሜን ኮርያ ፖሊስ ኪምን ለመምሰል የተሰፉ ልብሶችን ለብሶ መገኘት ከዚህ በኃላ እንደማይታገስ ፍሪኤዥያ ሬድዮ ዘግቧል።
ህብረተሰቡ የቆዳ ጃኬቱን እንዳለብስ መታገዱን ያሳወቀው ፖሊስ ማን መልበስ እንደሚችል መወሰን የገዢው ፓርቲ መመሪያ አካል ነው ብለዋል።ከዚህ ቀደም ኪም ጆንግ ኡን የፀጉር ስታይላቸው የሀገሪቱ ወንዶች ከእርሳቸው ጋር እንዳያመሳስሉ ከልክለው ነበር።
በስምኦን ደረጄ